November 21, 2024
22 mins read

ጠቅላይ ሚኒስቴሩ አልተስተምሮም

The title of the document is The Importance of Ministry Altimetry. Abiys Fake PHD 1.jpgጠ/ሚ እብይ አህመድ በዶ/ር መዐረግ ወደ ስልጣን ከመጡ ስድስት አመት አልፎቸዋል፡፡የጠ/ሚ ዶክትሬት ድግሪ መሰጠት ያልነበረበትና ከ62% በላይ ከሌላ የተቀዳ መሆኑን ፕ/ር አሌክስ ደዋል ከሌሎች ሶስት ባለሞያዎች ጋር ሆነው አረጋግጠዋል፡፡ ክፍል ገብተው ሲማሩም አንዳልታዩ ፐሮፌሰሩ ምልከታቸውን ገልጸዋል፡፡

አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ዶክትሬት ድግሪቸውን ይቀማቸው አይቀማቸው የሚለውን ትተን፤ በእውኑ ጠ/ሚ አብይ የሚያሳዩት ባህሪ አንድ በዶክትሬት ድግሪ  ደረጃ የተማረን ሰው ባህሪ ነው ወይ ብለን ስንጠይቅ መልሱ አልቦ-ዜሮ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

አንድ ሰው የማስትሬት ወይንም የዶክትሬት  ድግሪውን ሲሰራ ጽሑፍ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ በተለይም የፒኤችዲ ዲሰርቴሽን ከማሰተርስ ድግሪ ቴሲስ የሚለየው በይዘቱ የግል ምልከታና ምርምር (original) የሆነና በትንታኔ የዳበረ መሆን ስላለበት ነው፡፡

የዶ/ሬት ድግሪ ለመስራት ከሶስት እስከ ስምንት አመታት የሚፈጅ ሲሆን፣ ዕጩ ዶክተሩ በመረጠው ርዕስ ላይ የተጻፉ ጽሑፎችን ያነባል፣ይተቻል፣ ከእርሱ ስራ በፊት በተስሩ ስራዎች ላይ ያሉ ስህተቶችና እንከኖች ነቅሶ ያወጣል፡፡አዲስ ጥያቄ ያነሳል፤ መልሱንም የተለያዩ የትንታኔ ዘዴዎችን በመጠቀም ከድምዳሜው ላይ ያደርሳል፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥም ዕጩ ዶክተር ተማሪው የመጻፍና ከሰዎች ጋር የሚያደርገው የግንኙነት መስተጋብር ክህሎቶቹን ያዳብራል፡፡ ለዚህም ነው የዶክትሬት ድግሪ እንደው በያዝ ለቀቅ የሚገኝ ስላልሆነ ከፍተኛ ክብር ለባለቤቱ የሚያሰጠው፡፡

በሃገራችን ስለ ሙህር አንድ የሚባል እውነት አለ፡፡ይኸውም ሙሁር አንጻር ያበዛል ነው፡፡ ዶክተሩ በትምህርት ዝግጅቱ ግዜ ነገሮችን ከተለያየ አንጻር በመመልከት የቢሆን(Scenario) ትንተኔዎችን ስለሚስጥ በሁኔታዎችና ነገሮች ላይ የሚኖረው እይታ በአንጻር የተሞላ ነው የሚሆነው፡፡

ስለዚህም አንድ በዶ/ር ደረጃ ያለ ሰው አፉ እንዳመጣለት አይናገርም፡፡ አጠቃሎ በድምስሱ መናገር ላይ ይቆጠባል፡፡ የዶክትሬት ድግሪ ሲሰራ የተለየ ጥያቄ ላይ በመሆኑና በዘርፉ የተወሰነ ክፍል ላይ በጥልቀት በሚደረግ ምርምር ላይ የሚሰጥ የትምርት ማስረጃ በመሆኑ፣ በዶ/ሬት ደረጃ የተማረ ሰው በሙያው ላይ እንጂ በሌሎች ሙያ ላይ ገብቶ ከመዘባረቅ ይቆጠባል፡፡የግል አመለካከቱን የግሌ ብሎ ይሰጣል፡፡ የሰዎችን ስራና ጽሑፍ ምንጭ ጠቅሶ ያቀርባል፡፡

እስኪ አሁን ወደ ዶ/ር(?) አብይ እህመድ እንምጣ፡፡ በሁሉም የሙያ ዘርፎች ላይ ትንታኔ መስጠት አይታክታቸውም፡፡ የራሳቸው ያለሆኑ አባባሎችን እንደራሳቸው አድርገው ያቀርባሉ፡፡ ራሳቸውን ከምንዝሮቻቸው ጋር የሚያስተያዩት እንደ መንፈሳዊ መሪም ስለሆነ መብቂያ የሌላቸውን ምሳሌዎች ያበዛሉ፡፡ በዚህም ከባህል፣ ከሃይማኖትና ከፈጣሪ ጋር ሳይቀር ሲዘናቆሉ ይውላሉ፡፡

ሰሞኑን ጠ/ሚ አብይ ሰለ አበባየሆሽና ሆያ ሆዬ ባዕላት ግጥም መቀየር እንሚገባቸው በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብለው ነገሩን፡፡ እንደሚመስለኝ “…ትቆጣኛለች እንጀራ እናቴ …” የሚለው ስንኝ ላይ ትኩረት ያደረጉ ይመስላል፡፡ ለምን እንጀራ እናት በእኩይ ምግባር ተነሳች ነው የነገሩ ሽፋን፡፡

አንደኛ ጥሩ የሆኑ እንጀራ እናቶች እንዳሉ ሁሉ መጥፎ የሆኑም አሉ፡፡ ደግሞ ከስንት መቶ አመታት በፊት የተገጠመ ግጥም ላይ አርተኦት ማድረግ ምን ያሰፈልገዋል? በአለም ላይ በተለያዩ ባህሎችና ህዝቦች ዘንድ ለብዙ መቶ አመታት የተጻፉ ከአንድ ሺህ በላይ የእንጀራ እናት ታሪኮች  እንጀራ እናትን የሚገልጹት በእኩይ ሁኔታ ነው፤ የሆሊውድ ፊልሞችም እንደዛው፡፡

በዚህ ግጥም ውስጥ ኮኮብ ቆጣሪዋ ልጃገረድ አምሽቼ በመግባቴ እንጀራ እናቴ ተቆጣችኝ አለች እንጂ ምን አለች፡፡ እናቷም ብትሆን የደረሰች ልጅ ውጭ ስታመሽ መቆጣቷ አይቀርም፡፡ ይህ ውብ የሆነ ስነውበትን(Aesthetic ) በውስጡ የያዘ ዘፈን ስለ ገበሬ ቤተሰብ የሚያትት፣ የፍቅር ህይወትን፣ ቤተሰብ መመስረትን ተሰፋ የሚደርግና ልጆች ከቤት ቤት እየሄዱ ወለጆችን የሚመርቁበት የባህል ዘፈን ነው፡፡

ጠ/ሚሩ እውነት የፒኤችዲ ተማሪ ቢሆን ኖሮ ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣውን የህብረተስብ እምነት፣ እሴትና ቅቡል ዋጋ እንዲሁም የማይዳሰሰውን ባህል(Intangible Culture) በስነሰብ( Anthropology and Folklore) ለመመዘን ይሞክሩ ነበር እንጂ በዚህ ደረጃ ወርደው አይቆነጽሉም ነበር፡፡ ይህን የሰሜኑ ኢትዮጵያ ክፍል መገለጫ ነው ብለው ያሰቡትን ባህል የሚዋቀስና ረብ የለሽ የሚያደርግ ሃሳብ ከመሰንዘር ይቆጠቡም ነበር፡፡

ቡሄም እንዲሁ ተመሳሳይ ነው፡፡ ከእብራውያን ባህል ጋር ተሰናስኖ የሚተረጎም ነው፡፡ መሬት የሚደቃውም ዱላ ከጥንት የበሬው እግር ድምድም ሚቶሎጂ ጋር ተይዞ የሚተረጎም ነው፡፡ ታዲያ እነዚህ በነሃሴና መስከረም ግዜ የሚዘፈኑት ዘፈኖች የጠ/ሚሩን አይን ምነው አቀሉሳ? ነገ ደግሞ አሸንዳይ ላይ መውረዳቸው አይቀርም፡፡

አበባየሆሽ ብዙ ነገርን የሚያጣቅስ የባህል መገለጫ ነው፡፡ አበባየሆሽ የሚዘፈንበት የዘመን መለወጫ፣ እንቁጣጣሽን ንግስት ሳባ የንጉስ ሰለሞንን ጥበብ ለመፈተን በሄደችበት ወቅት ለጣቷ እንቁ ሰጥቷት ስለነበር እንቁ ለጣትሽ ከሚለው ቃል የተቀዳ ነው የሚለው ሃሳብ በኢትዮጵያ ሊቃውንት ዘንድ አዘውትሮ ሲነገር ይሰማል፡፡

ሌላው በዚህ ዙሪያ የሚነገረው ስለ የጥንቷ ኢትዮጵያዊት ንግስት ካሶጵያ ነው፡፡ ንግስት ካሶጵያ የልጇ አንድሮሜዳ ውበት ከሁሉ እንደሚበልጥ በተከራከረች ግዜ፣ የባህሩ ዘንዶ ንጉስ የኢትዮጵያን መሬት ሊያጠፋ ተነስቶ ዙሪያዋን አወደመ፡፡ በዚህን ግዜ ካሶጵያ ልጇ አንድሮሜዳን ለባህሩ ዘንዶ ለመገበር በአለት ላይ አስራ መስዋት አቀረበች፡፡

ነገር ግን ፔርስዌስ የተባለ ጀግና የባህሩን ዘንዶ ንጉስ እራስን ቆርጦ አንድሮሜዳን በመታደግ አዳናት፣ ከዚያም አግብቷት ስድስት ልጆች ወለዱ፡፡  እንግዲህ አንድሮሜዳ በጥንታውያኑ ዘንድ ህብረክዋክብት በሰሟ ተሰይሞላት፡፡ ህብረክዋክብቱ (Constellation) በሰሜን ንፍቀ ክበብ ለምንገኝ ኢትዮጵያን ከነሃሴ ወር ጀምሮ በጠቆረው ሰማይ ላይ በአይናችን የሚታያ ነው፡፡

ታዲያ አበባየሆሽ ጨፋሪ ልጃገረዷ፣ ልጇን ለመሰዋእት ያቀረበች የኢትዮጵያ ንግስት ካሶፒያንና አንድሮሜዳን በህብረ ክዋክበቱ የሰማይ ሰሌዳ ላይ እያየችና እያሰበች አንድሮሜዳን መሆንን እየናፈቀች፤

እደጅ አድራለሁ ኮኮብ ስቆጥር

ኮኮብ ቆጥሬ ስገባ ቤቴ

ትቆጣኛለች ችንጀራ እናቴ

ብትል ምን ነገር አለው? እንደ ፔርሱዌስ ያለ ባልም ለማግባት፣ አፈ ንጉስ ባል እየናፈቀች ብትዘፍንስ ምን ገዶን፡፡

ቀረብ ያለው የሃገሯ ታሪክ የሚነግራት ደግሞ አንጋቦ የሚባል የንጉስ ዘር ያልሆን ጀግና እባብ አርዌ የሆነውን የአክሱም ንጉስ ገድሎ የንግስት ሳባን ዙፋን አስቀጠለ የሚል ነው፡ ፡ይህ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ የአማልክት ትርክት ትእምርት ኢትዮጵያ በጥንቱ አለም አስትሮኖሚ ውስጥ የነበራትን ቦታ የሚያሳይ እንጂ የሚነቀፍ አይደለም፡፡

ሌላም አለ፤

ጨረቃ ድንቡል ዶቃ

አፄ ቤት ገባች አውቃ…

አሊሆይ አላሊሆይ

ውድ አባቴን አያችሁ ሆይ?

ውድ አባቴን ያያችሁ፣

ሚስጥር አለኝ ልንገራችሁ…

ይህ ደግሞ ንግስት ሳባ ከንጉስ ሰለሞን ቀዳማይ ሚኒሊክን ፀንሳ ወደ ሃገሯ ከተመለሰች በኋላ፣ለወለደችው ልጇ አባቱ የሰጠውን ቀለበት እያሳየችው ነው ያሳደገችው፡፡ እሱም ወደ እየሩስአሌም ሄዶ አባቱን እሰከሚያገኘው ድረስ በእብራይስጡ “አሊሃ” መለትም ወደ ትውልድ ስፍራ መመለስን እየዘፈነ ነው ያደገው፡፡

አሊሆይ ማለት አሊሃ ሆይ ማለት ነው፡፡ ሆይ መለት ደግሞ ማጋነንን የሚያሳይ ቃል ነው፡፡ ጃን ሆይ እንደማለት ወይም ጃን(ታላቅነትዎ) ሆይ እንደ ማለት፡፡ እንግዲህ በሰሜኑ ኢትዮጵያ ክፍል በልጆች አንደበት የሚዘፈኑ የአመት ባዕል ዘፈኖች እንዲ የመሳሰለ ታሪካዊና ባህላዊ ዳራ አላቸው፡፡

ታዲያ ጠ/ሚ አብይን እንዲህ አይናቸውን የሚያጉረጠርጥባቸው ነገር ከየት መጥቶ ነው ካልን የሴማዊ ህዝብ ድብቅ ጥላቻ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ መጽሐፋቸው “እርካብና መንበር” ላይ በግልጽ አስቀምጠውታል፡፡ አንበሳን ከኢትዮጵያውያን ነገስታት ጋር ደህና አድርገው አበሻቅጠው ነው የጻፉት፡፡ በተለይም ሞአ አንበሳን ይጠሉታል፡፡ ምክነያቱም ስሩን ከንጉስ ሰለሞንና ንግስት ሳባ ይመዛልና፡፡ አንበሳ በኢትዮጵያ ባሉ ባሎች ሁሉ የተከበረ ነው ሌንጮም ይባል ሌላ፡፡ ጠ/ሚ አብይ የአንበሳውን አርማ አጥፍተው በኢትዮጵያ በማትታወቅ ወፍ-ፒኮክ ከቀየሩት ሰንብተዋል፡፡ ጠ/ሚሩ የፖለቲካ ዳፍንት ባይዛቸው ኖሮ አንበሳ የፊውዳል ኢትዮጵያ አርማ ብቻ ሳይሆን በአውሮፓ፣ አረብ፣ ኢራን…በተመሳሳይ ትረጉም የነበረ መሆኑን ይረዱ ነበር፡፡

የንግስት ሳባን ትርክት አጥብቀው ይጠላሉ፡፡ እራሳቸውን ደግሞ እንደ ሙሴና እየሱስ እየመሰሉ በየባዕላቱ ሲቦተልኩ ይውላሉ፡፡ በ2014 ዓ.ም. ጥር ወር ላይ በምርጫው አሸንፌለሁ ብለው በፓርላማ ቃለ መሃላ ሲያደርጉ “አዲስ ምእራፍ” (New Beginning) በሚል ርዕስ አስር ቅጠሎች ያሉት አደይ አበባ ከተማዋን እጥለቅልቖት ነበር፡፡ ምኑ ቅጡ ቢጫ የሆነ የህንፃ አርቲቴክቸርም ተሰርቶለታል፡፡ እዚህ ላይ እንግዲህ አደይ አበባ የእሳቸው ብቻ መሆን እንዳለበት የሚያስመለክቱን፡፡

ጠ/ሚ አብይ ለሳቸው ፖለቲካ የሚሆን መፅሐፍ ቅዱሳዊ ታሪክ ሲቃርሙ ደስ የማይላቸው ታሪክ ያገኛሉ፡፡ ማቴዎስ ወንጌል ም.12፣42፡፡

“ኝግስት ሳባ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስታ ትፈርድበታለች፤የሰለሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር ወጥታለችና፣እንሆም ከሰለሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ፡፡ እዚህ ጥቅስ ላይ ማቴ 6፣28-29 ጨምሩበት፡፡

“ስለ ልብስ ለምን ትጨነቃላችሁ? የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ  ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፡፡ አይደክሙም አይፈትሉም ነገር ግን እላችኋለው፣ ሰለሞንስ እንኴን በክብሩ ሁሉ ከእነዚህ እንደ አንዱ አለበሰም፡፡”

ጠ/ሚሩ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የሚጠሉትን የፈራጇን ንግስት ሳባና ንጉስ ሰለሞን ታሪክ ካነበቡ በኋላ አበቦች ከንጉስ ሰለሞን የበለጠ መልበሳቸው ያጽናናቸዋል፡፡ ከሰለሞን የበለጠ ደግሞ እዚህ አለ ተብሎ አይደል፣ እሳቸው በእሱ ትርክት ውስጥ ራሳቸውን የሚገልፁበት እያሱስ ታለቅ ነው ተብሎም መጠቀሱም ለሴማውያን ላላቸው ጥላቻ አንጀት አርስ ማጣቀሻ ነው፡፡እንግዲህ  ጠሊቁ የሰነልቦናቸው ምስቅልቅልዮሽ ድርና ማግ እዚህ ላይ ነው የተሸመነው፡፡

ይህም በውስጥ ግጭት ስለሚፈጥር የሰሜናዊው ባህል መገለጫ የሆነው ስንኞቹ በአደይ አበባ የተሽቆጠቆጡት ንግስት ሳባንና ንጉስ ሰለሞንን የሚተረከውን የአበባየሆሽ ባህል ይጠሉታል፡፡ ፈቀቅ እንዲልላቸውም ይፈልጋሉ፡፡ በቃ እሳቸው የኢትዮጵያ አዲሱ ዘመን አብሳሪ፣ ፈር ቀዳጅ፣ ቢጮሌ አሻጋሪ፤ መልካቸው በሰማይ ሰሌዳ ላይ ወገግ ብሎ የሚታይ አድርገው ነው  እራሳቸውን መሳል የሚፈልጉት፡፡ ይሀው ነው ታሪኩ፡፡ እዚህ ላይ ነው የሰነልቦነቸው ቀውስ ፍንተው ብሎ የሚወጣው፡፡

አሁን ደግሞ ከፍ ብለው እስልምናና ክርስትና ለዚህች ሃገር ምንም ለውጥ አለማጡም ይሉናል፡፡ ከመቶ አመት በፊት አፄ ቴውድሮስ፣ አፄ ሚኒሊክ፣ ንጉስ ሳህለ ስላሴ፣አጼ ዮሐንስ የእንዱስተሪውን አብዮት ከጃፓን እኩል ጀምረው እንደነበር ቢያነቡም፣ ማስረጃዊችን በአይናቸው ቢያዩም፣ አይገባቸውም፤ እሳቸው የመጀመሪው መሆን አለባቸውና፡፡

የሆነስ ሆኖ ወንድሜ የሚሉት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች  ሼክ ከሃምሳ አመት በፊት በሰንበሌጥ የተሰራ ዳስ ውስጥ አያቶቹ ያድሩ እንደነበርና መሬት ላይ ቁጭ ብለው ይበሉ እንደነበር ፊልም ብናሳያቸውም አይቀበሉንም፤ መቼ የእኔነት አባዜ በቀላሉ ይለቃልና፡፡ኢትዮጵያ ለለአለማደጓ ሃይማኖትን ተጠያቂ የሚያደርጉ፣ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚን በግዜ ወደ ኋላ ሄዶ ለማየት ቅድመና ድህረ ቀኝ ግዛት ኢትዮጵያ፣ ኮሚኒስቷ ኢትዮጵያ የማትታያቸው፣ በግጭት አፈታት ላይ ዶክትሬት ድግሪ ይዤለሁ የሚሉት አብይ ምንኛ አልቦ – ዜሮ ናቸው፡፡

አንዳንድ ግዜ ጠ/ሚ አብይ ስለ ዛፍ፣አእዋፋት፣ ውሃ፣ ዶሮ ወጥና ሽንኩርት፣ ጎመን በጨው፣ ዳቦና ማር፣ ኋላና ፊት አይን፣ …ባጠቃላይ ስለ ሰማዩም፣ ምድሩም፣ እንስሳቱ፣ አእዋፍቱ…በቦታውም ያለቦታውም ሲናገሩ ስሰማ እኚህ ሰው ከንጉስ ሰለሞን ጋር ፉክክር ይዘዋል እንዴ እላለሁ፡፡ የስነልቦና ቀውስና ምስቅልቅሎሽ (Physiological disorder) ይሉሃል ይሄ ነውና፡፡

እንዲህም ተብሎ በታላቁ መጽሀፍ ተጽፏልና፤ 1ኛ ነገ 4፣ 30 – 33 “የሰለሞን ጥበብ በምሥራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ጥበብና ከግብጽ ጥበብ በለጠ፡፡…ስለዛፍም ከሊባኖስ ዝግባ ጀምሮ በቅጥር ግንብ ላይ እስከ ሚበቅለው እስከ ሂሶጵ ድረስ ይናገር ነበር፤ ደግሞም ስለ አውሬዎችና ወፎች ስለ ተንቀሳቃሾችና ስለ ዓሣዎች ይናገር ነበር፡፡”

እንግዲህ ስነሰቡን፣ኢኖሚክሱን፣ስነውበቱን፣ ወታደርነቱን… ሁሉን እንዲህ በወረደ ሁኔታ የሚያይ አእምሮ በፒኤችዲ ተለንቁጦና ተሟሸቶ ነበር ቢሉን መቼም ፌዝ ይሆናል፡፡ ጠ/ሚ አብይ እንኴን የፒኤችዲ ዲሰርቴሽን አይደለም የመጀመሪያና ማሰተርስ ድግሪ ቴሲስ ላይ ያልተመራመሩ፣ ከልምድና ተሞክሮ እንኳን የልተማሩ አፈና እግረ ተማሪ ናቸው፡፡

 

አስቻለው ከበደ አበበ

ሜትሮ ቫነኩቨር ካናዳ


 

Abiy Ahmed’s Fake PHD

5 Comments

  1. Regarding Abebayehosh song:
    Abiy’s problem seems to be mainly with three elements he specifically mentioned in the song:
    1. Bet sisera
    His wish is not for her to build a house but for her house to be destroyed. House is a metaphor for nation. [ምኞቱ ቤት እንድትሠራ ሳይሆን ቤቷ እንዲፈርስ ነው። ቤት የሀገር ምሳሌ ነው።]
    2. Injera
    Here, his mission is to make Ethiopians stop eating injera and totally be dependent on the unhealthy American wheat. እዚህ ላይ ተልእኮው ኢትዮጵያውያን እንጀራ መብላት አቁመው ጤናማ ባልሆነው የአሜሪካ ስንዴ ላይ ጥገኛ እንዲሆኑ ማድረግ ነው።
    3. Inat
    He is against the mother image of Ethiopia (የኢትዮጵያን የእናትነት ገጽታ ይቃወማል)
    If Abiy Ahmed is playing dumb and trying to misrepresent the Abebayehu song, here is a link to another Oromo intellectual, Mr. Zemedu, who has beautifully rendered the poetic and layered meaning of the ancient Abebayehu song. Zemedu’s beautiful interpretations predate Abiy’s sinister (or dumb, as you wish) insinuations about the Abebayehu song by a solid three years!
    Abiy may also be against “Bale Injeroche gibu betera”. He does not want her calling her compatriots into her country. He is expecting his masters from across the Red Sea to populate the resorts, and the externally bling-bling internally stinking bubble he is building.
    Here is a modified Abebayheu to be sung at the palace for the Surpreme Telalaki, the black Graziani.

    አበባየሆሽ
    አበባ አየሽ ወይ? የለም!
    እንጀራ አየሽ ወይ? የለም!
    እውነት አየሽ ወይ? የለም!
    እምነት አየሽ ወይ? የለም!
    አቢይ አህመዴ አዎ
    ዘር ሲመነጥር አዎ
    እንኳን ቤትና አዎ
    የለኝም አጥር አዎ
    እደጅ አድራለሁ አዎ
    ቀኑን ስቆጥር አዎ
    የፋኖ መምጫ አዎ
    ሆኖብኝ ምስጢር አዎ
    በመስከረም ነው? አዎ
    አለዚያስ በጥር? አዎ

    አደይ የብር ሙዳይ ኮለል በይ
    አደይ የብር ሙዳይ ኮለል በይ

    እቴ አበባ እቴ አበባዬ አዬ! እቴ አቤቤዬ
    እቴ አበባ ስትለኝ ከርማ አዬ እቴ አቤቤዬ
    ቤት አፍርሳ ባምሌ ጨለማ አዬ! እቴ አቤቤዬ
    እደጅ ጣለችኝ አዳነች ኡማ አዬ! እቴ አቤቤዬ
    ያየውን ሁል የሚለው ኬኛ አዬ! እቴ አቤቤዬ
    አባት ዳኛ ልጁ ቀማኛ አዬ! እቴ አቤቤዬ
    አዬ! እቴ አቤቤዬ (X4)

    ከስረው ይቆዩኝ ከስረው
    እጆን የፊጥኝ ታስረው
    ከእምዬ ዙፋን ወርደው
    ቂሊንጦ ገብተው ለምደው
    ከስረው ይቆዩኝ ከስረው

  2. ታዲያ ይህ የተገለበጠውን ፒ.ኤች.ዲ. ጽሑፍ ለአብይ ማን ሰራለት ? ከነዚህ ከጠቀስካቸው ግጥሞች ሌላ ክታሪክ ጋር የተያያዘ ዘፈን አለ ወይ? በተረፈ እፁብ ድንቅ ነው::

  3. ይገርማል ቀለል አድርገህ ጀምረህ እንደ ቦይ ውሃ በፈለግኸው መንገድ ወሳሰድከን። ለነገሩ ይህ ፒ ኤች ዲ ተብሎ ፈረንጅ ለማወቃቸው የሚሰጣቸውን ማረጋገጫ መቀበል ካቆምኩ ሰነባብቻለሁ። አሁን ብርሃኑ ነጋ በአማርኛም ሆነ በእንግሊዝኛ ሲያስረዱ የሰማ ሰው እንኳን ከአፋቸው የሚወጣውን ቁም ነገር ለመከተብ ቀርቶ የጤንነታቸውም ሁኔታ ያስጨንቀዋል። አንድ ሰአት ቁጭ ብለው ዩ ኖው አሚን እያሉ ጠረቤዛ ከመደለቅ ያልሆነ ምሳሌ ከመስጠት አይን ከማፍጠጠ ባለፈ ላዳማጭ አንድ ረብ ያለው ነገር ሲያስጨብጡ ተሰምተው አይታወቁም።

    በተረፈ ጸሃፊው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የዶር አብይን ዱፍትርና ይሰርዝ ያልከው ውስጥ ለውስጥ ማጠናከሪያውን ይሰራ እንደሆን እንጅ አይቀማቸውም ምክንያቱም ብርሃኑ ነጋ ስርአት ተላልፎ የትምህርት ሚኒስቴር እና የዩኒቨርስቲው ቻንስለር ሲሆን መጠርጠር ይገባ ነበር። ብሬ ተደጋግሞ እንደታየው የኢንተግሪቲ ጉዳይ ባጠገቡ አያልፍም ዶር አብይ ለቦታው ባይመጥንም ለሰጡት ሹመት በአይነት ይከፍላቸዋል እናንት ግን ነቃ ብላችሁ ጠብቁ።

    ግራ የገባ ጉዳይ ነው አብይ ዶፍተር ካልሆኑ ምን ብለን እንጥራቸው ይህንንም ብታመላክተን ጥሩ ነበር። ግራ የገባው ጊዜ አቶ ዳንኤል ክብረትን ዲያቆን ስንለው ከርመን ባለፈው በጴንጤ ዳንኪራ ተመልካቹን በጭፈራ ሲያደስተው አሳዩን ለሱም እንዲሁ አንድ መጠሪያ ጀባ በለን።
    ፍትህ ለታዲዮስ ታንቱ፤መስከረም አበራ፤ክርስቲያን ታደለና ለሌሎች…

  4. Ngsti when you read Amharic articles think the way the language speakers think. I don’t think you have understood what the writer wanted to pass. Your objective is to initiate others to stand against him. The room is different from Tegarus men are judged on thier intellectual calibre.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop

Don't Miss

GduIqzWXMAAO9M

ጠቅላይ ሚኒስቴሩ አልተስተምሮም ቁ.2

ጠ/ሚ አብይ “ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል ” የሚለው አባባል ላይ