እኝህ በፎቶግራፉ የሚታዩት ከበርቴው አላሙዲ ከረጂም እገታ በኋላ ለመመለሳቸው በሶሻል ሚዲያና በአርቲስት ተስፈኞች በስፋት ሲናፈስ ከርሞ አዲስ አበባ መምጫቸውን በጉጉት በመጠባበቅ ላይ ትገኛለች። የእኝህ ከበርቴ እገታ እኛው አገር በኦነግ ሸኔና በመንግስት ከሚደረገው ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ ካሁን በኋላ በሃገራችን የሚደረገውን እገታ ሸሁ አጥብቀው ይጠየፉታል ብለን እናምናለን።
ዶር አብይ ወደ ስልጣን እንደመጡ አዲስ አበባ መቀመጥ በጣም ጠልተው ነበር መሄድ ነው መሄድ ነው ማውራት ነው ማውራት ነበር። የሃገር ቤቱ ሲሰለቻቸው ወደ ውጭ በመሄድ በሳውዲ ባደረጉት ጉብኝት ቢንዛይድን አነጋግሬዋለሁ ዛሬ ወይም ነገ ሸህ አላሙዲ ወደ አገራቸው ይመጣሉ ብለው ነግረውን የሸሁን መምጣት ለሚጠብቁ ታላቅ ፈንጠዚያ ሆኖ ነበር። ነገር ግን ጊዜ እያለፈ ሲሄድ የ ጠ/ሚኒስትሩ ጥያቄ ይፈታልኝ ይሁን ትንሽ እሹልኝ በቦታው ስላልነበርን እውነታውን መመስከር አልቻልንም ያ ባይሆን በነጋታው ይመለሳሉ የተባሉት ሰው እንዴት ይህን ያህል ጊዜ ሊቆዩ ይችላሉ? መቼም ብዙ ነገር ካየን በኋላ ዶር አብይን ማመን እጅግ ከብዶናል እንዳጋጣሚ ሁኖ አንዱም እውነትነት አልታየበትምና።
በእርግጥ የጀማል ካሾጊን የመሳሰሉ የሃገሩን ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ አምላክ የፈጠራትን ነብስና ስጋ ከታትፎ ገድሎ አላህ አኩበር ከሚለው አረመኔ መንግስት በኢትዮጵያ አምላክ እገዛ ተርፈው ወደ ተስፋይቱ ምድር ኢትዮጵያ ከተመለሱ እንኳን ደስ አሎት ሊባሉ ይገባቸዋል። ፡፡ የሸሁን መፈታት ተከትሎ ለአቀባበላቸው 600 000 ዶላር የሚፈጅ ሮልስ ሮይስ መኪና ወደ ጉምሩክ ደርሶ የኦሮሙማ ባለ ስልጣኖች ይህ ለከፍተኛ የኦሮሙማ መስፍኖች ካልሆነ አንለቀም በማለት ትልቅ ውዝግብ ፈጥረው እንደነበረ በሚዲያ ተመልክተን ነበር። እንግዲህ የኦሮሞ ከፍተኛ ባለስልጣን ማለት ወይ ሽመልስ አብዲሳ ወይ አብይ መሃመድ መሆኑ ነው። አረጋ ከበደን ሙስጠፌ መሃመድን አወል አርባን….. ማን ሰው ብሏቸው።
የአዲስ አበባን ነዋሪ ሲፈልጋቸው ሲቀሙ፤ ሲያንገላቱ፤ሲገድሉ እንደከረሙ ሁሉ የሸሁን ንብረት መቀማት አሁን ላለባቸው ለዶላርና ተመሳሳይ ችግር ክፉ አደጋ ላይ የሚጥላቸው መሆኑን የኦሩሙማው ባለ ስልጣኖች ስለ ተረዱ እርምጃቸውን አዘግይተውታል። ሆኖም የአይን እማኞች እንደሚሉት መኪናውን በማይገባ አጠቃቀም እኛም እንሞክረው፤ መሪውን ይዘን ፎቶ እንነሳ በሚል ጅልነት አውቶሞቢሉ ውስጥ ተራ በተራ በመግባት አውቶሞቢሉን ስላጎሳቆሉት የመጀመሪያ ይዞታውን አለመያዙን በስፋት ይወራል፡፡ ይህ እንኳን ብዙ ቁም ነገር ያለው ባይሆንም የዘመኑ ባለስልጣኖች ነገር ስራቸው ሁሉ ለአቅመ አገር ለማስተዳደር እንደማይበቁ ለማሳየት በማዳበያነት የቀረበ ነው።
ሼህ አላሙዲ የሚዲያና የውይይት ቀልብ ይስባሉ ስለ ልግስናቸው የሚወራው መቼም አይጣል ነው። አቶ እከሌን መጨበጣቸውን የተመለከት ወሬ አናፋሽ ባይኔ በብረቱ አየሁ እድለኛውን ኬሻ ሙሉ ብር አሸክመው ላኩት ይላል፡፡ በመንገድ ሲያልፉ የወጣቱ ጥረት ስለሳባቸው ወደ ባህር ማዶ ልከው አስተምረውት የአንዱ ድርጅታቸው ስራ አስኪያጅ አድርገውታል ይልሃል ሌላው ምናባዊ ወሬኛ ፤አርቲስቶች ለተባሉትማ ሰጡ የሚባለው ሲሰማ ጆሮ ጭው ያሰኛል ሰውየው ከተራው ህዝብ ጋር አብረው ለመሆን ችግር እንደሌለባቸው ግን እኛም በርቀት ታዝበናል።
ዛሬ ስለ ሼህ አላሙዲ ልናነሳ የተገደድነው ዋናው ፍሬ ነገር ሸሁ ቀደም ሲል የኢትዮጵያን ህዝብ አጥንትና ሃብቱን የጋጠውን የብዙ ዜጎችን ህይወት የቀጠፈውን የትግሬን ነጻ አውጭ ሽፍታ በጎደለው ክፍተት እየሞሉ ምርኩዝ ሁነው ሃገርና ወገን ላይ የደረሰውን በደል ዛሬ ላይ ዜጎች እንዳልረሳነው ለማስታወስ ያህል ነው፡፡ በአንድ ወቅት በግላጭ ዝንብ ይሁን ንብ የህወአትን መገለጫ መለያ ቲ ሸርት ለብሰው ህዝብን በመናቅ የሰጡትን አስተያየት ዛሬም ከዜጎች አእምሮ አልተፋቀም። ከአጋዚ አለቆች ከነስብሃት ነጋ ጋር በአንድ አስርሽ ምችው ፓርቲ ላይ ንፋስ እንዳይገባቸው ተገጣጥመው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሲያላግጡም አይተን ታዝበናል። ሸሁ ከአረመኔዎቹ ከነ ስብሃት ነጋ፤መለስ ዘራዊ፤አርከበ እቁባይና መሰል የትግሬ ፋሽስቶች ጋር በፌሽታ ላይ ፍቅር በፍቅር ሁነው ሲፍነቀነቁ በተለያዩ ምስሎች ተቀርጾ ተለቋል፡፡ ዛሬ እነዛ ለሰማይና ለምድር የከበዱ አረመኔ የትግሬ ገዥዎች ከተደበቁበት ተበለሻሽተው ከጎሬያቸው በመከላከያ ሃይሉ ተጎትተው ሲወጡ ነገሮች ባሉበት እንደማይቀሩ ለሸሁ ትምህርት ይሰጣል ብለን እንገምታለን። ምድሪቱ የምታስተምረን ግፈኞች የሃጢያታቸው ስበት ሲያመዝን እንደዚህ ተዋርደው በህዝብ አይን መበላታቸው የታሪክና የተፈጥሮ ሀቅ ይሆናል በነሱም ምክንያት ወዳጆቻቸው ልጆቻቸው አብረዋቸው የሰሩ ሁሉ እንዳቀረቀሩ ይቀራሉ። እንግዲህ ካለፈው በመማር ዛሬም እንዲህ ዜጋን ልብ የሚያደማ ነገር በድጋሚ ከኦሮሙማ ግፈኛ ሹሞች ተዳብለው አገርን የሚጎዳ ነገር ይሰራሉ ብለን አንገምትም። ነገር ግን የተፈጥሮን ህግ ንቀው የኢትዮጵያን አምላክ ተጋፍተውና ታብየው በፍቃዳቸው ከሄዱ የህዝብ ሃዘን ያደረሰውን ለመታዘብ በቂ እድል የተሰጣቸው ይመስላል
አላሙዲ ኢትዮጵያን ይወዳል የሚሉ አሉ እውነት ከሆነ እናመሰግናለን ነገር ግን አፋኝ ስርአቶችን የጎደላቸውን እየሞሉላቸው ግፍና ጭቆናን ምድሪቱ ላይ የሚያሰፍኑ ከሆነ አጥብቀን እንቃወማለን። በቀጥታና በተዘዋዋሪ የራሳቸውንና እስላማዊ የአረብ አጀንዳ ይዘው ያንን ለማስፈጸም የተለያዩ እንቅስቃሴ ከሚያደርጉ ወንጀለኞች ጋር በገሃድም ሆነ በስውር የሚሰሩ ከሆን አንድ አይናችንን ጨፍነን እንመለከታለን። በመጨረሻ ግን ህዝብ አሸናፊ መሆኑን ማስገንዘብ እንወዳለን፡፡ ዛሬ ከትግሬዎች የቀጠለው የኦሮሙማ መንግስት ከሃገርም ከውጭም ውግዝ ካሪዮስ ሁኖ ባለበት ሁኔታ ህዝቡ ሃይል አስተባብሮ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊንደው በመንደርደር ላይ እያለ አላሙዲ ይህን ሃይል ለማቆም ያላቸውን ሃብት፤እውቅና ፤የውጭ ትስስር በመጠቀም ትግሉ ላይ ውሃ ሊቸልሱ ከሞከሩ ሁል ጊዜ የተገፋ ሃይል አሸናፊ በመሆኑ ለሁለተኛ ጊዜ ይህንን ስርአት ደግፈው ዳግም ስህተት እንዳይሰሩ አጥብቀን እናሳስባለን፡፡
አላሙዲ ባለሃብትና መዋእለ ንዋይ አፍሳሽ ናቸው አንድ ባለሃብት ከሚያደርገው ህጋዊ አሰራር ውጭ ከቆሸሹ በደም ከታጠቡ ነብስ ካጠፉ መሪዎች ጋር በመሆን የህዝብን ሰቆቃ ማብዛት ለክብራቸው አይመጥንም ብለን እናምናለን፡፡ እሳቸው ሲደግፉት የነበረው የህወአት አገዛዝ ኢትዮጵያውያን ላይ ያደረሰውን በደል ዛሬ ከዚህ ጽሁፍ አቅራቢ በላይ ስለሚያውቁት ወደኋላ ሂዶ ማስታወስ አያስፈልግም። አዲሶቹ ገዥዎቹም ቢሆኑ ለሸሁ ቀና ልብ እንደሌላቸው ማስገንዘብ እንወዳለን። በሚሊዮን የሚቆጠሩ አማራዎች በአይሁድ ያልደረሰው ስቃይ ወርዶባቸዋል የአላሙዲም እናት ዛሬ ከወሎ ተጉዘው ወለጋ ቢሰፍሩ የዛሬን ተውኝ ሁለተኛ አማራ አልሆንም ቢሉም መገደላቸው አይቀሬ ነበር ስለሆነም ከዚህ ስርአት ርቀታቸውን ጠብቀው ቢጓዙ መልካም ነው እንላለን።
ባጠቃላይ ሸሁ ከባለ ስልጣኖች ጋር የሚኖራችው ግንኙነት ላይ ገደብ መጣል ይኖርባቸዋል ግንኙነታቸው ፖለቲካዊ ሳይሆን ኢኮኖምያዊ መሆን ስለሚገባው እነሱ የሚያዙትን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከመፈጸም መቆጠብ ያስፈልጋል። ዛሬ የአማራ ባለሃብቶች የተባረሩት፤የተቀሙት ፤ተገፍተው ዳር የደረሱት አብይ መሃመድ አበባ ውሃ የማጠጣበት ይሄን ያህል ሚሊዮን አምጡ፤የአዳነች አቤቤን የሽመልስ አብዲሳን የልደት ቀን ለማከበር ይሄን ያህል ሚሊዮን አምጡ እየተባሉ ፍዳቸውን በሚያዩበት አገር ለሸሁ ከመንግስት የሚደረገው እንክብካቤ ጤናማ ባለመሆኑ ነቃ ብለው ምክንያቱን ሊመረምሩ ይገባቸዋል። ዶር አብይ በመጻፋቸው እንደገለጹት የሚፈልገውን ስጠው ከዛ ወደ ገደል ጨምረው እንዳሉት ሁሉ ሸሁ ቅድመ ጥንቃቄ ካላደረጉ መጨረሻው የጤና አይመስልም።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
ሰመረ አለሙ
semere.alemu@yahoo.com